Announcement የተመራቂ ሰልጣኞች የሶፍት እስኪል ስልጠና ተሰጠ

የተመራቂ ሰልጣኞች የሶፍት እስኪል ስልጠና ተሰጠ

24th July, 2025

የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የስራ ትስስርና ካውንስሊንግ ክፍል በኮሌጁ በሚሰጥ የተመራቂ ሰልጣኞች የሶፍት እስኪል ስልጠና ተሰጠ 

ከሰኔ 30/10/2017 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 04/11/2017 ዓ.ም 

የኮሌጁ የስራ ትስስርና ካውንስሊንግ ክፍል የተመራቂ ሰልጣኞች የሶፍት እስኪል ስልጠና የሰጠ ሲሆን በኮሌጁ  የስራ ትስስርና ካውንስሊንግ አስተባባሪ ፣በኮሌጁ የጥናትና ምርምር አስተባባሪ ፣በኮሌጁ የቢዝነስ ዲፓርትመንት ተጠሪ እና አሰልጣኝ እና በኮሌጁ የአይሲቲ አሰልጣኝ አማካኝነት ለ 5 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ።

በመቀጠልም የኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ዚያዱ ከማል የተሰጠው ስልጠና በቀጣይ ከስራ ጋር ለሚተሳሰሩ ሰልጣኞች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥርና ስራዎችን በእውቀትና ክህሎት እንዲሁም በአመለካከት ለመስራት የሚያስችል ስለሆነ በተሰጠው ስልጠና መሰረት የተለዩ ክፍተቶችን እያረሙ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በመጨረሻም እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎችን ለተመራቂ ሰልጣኞች መስጠት አስፈላጊ መሆኑንና ሰልጣኞችም ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with