ሀምሌ11/11/2017 ዓ.ም
የካ ኢንዱስትሪያል ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
በኮሌጁ የ2017 በጀት ዓመት የ4ቱም ሩብ ዓመት ማለትም የ12 ወራት የዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርት የኮሌጁ ኮር አመራሮች ዳይሬክተሮች ቡድን መሪዎችና ሁሉም የኮሌጁ ማኅበረሰብ በተገኘበት ማቅረብ ተችሏል::
የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርቱ በኮሌጁ የእቅዶና በጀት ቡድን መሪ የቀረበ ሲሆን የሁሉንም ዘርፎች እቅድ አፈፃፀም መሠረት ባደረገና ኮሌጁ በተያያዥነት የሰራቸውን ተግባራት መሠረት ባደረገ ነው።
የኮሌጁ ማኅበረሰብ በቀረበው ሪፖርት ላይ በተቋማት ልማት በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎች እንዲሁም በቴክኖሎጂና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ በጥንካሬ ተሰርተው ውጤታማ የሆኑትን ተግባራት በመዘርዘር በሪፓርቱ ተሠርተው ያልተካተቱ እና በቀጣይ ማስተካከያ ሊደረግባቸውና አፈፃፀማቸው ሊዘምኑ የሚገቡ ነጥቦችን በማንሳት ጠንካራ ተሳትፎ አድርገዋል።
በተጨማሪም የኮሌጁ ኢንተርፕራይዝ በከተማ ግብርናና በፈርኒቸር ውጤታማነቱን አስቀጥሎ መሄዱና ከኮሌጁ ማህበረሠብ በዘለለ ምርቶቹን ለውጭው ማህበረሰብ ማሣደጉ የሚበረታታና ሊቀጥል የሚገባ ተግባር መሆኑን ጠቅሠዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ኮር አመራሮች በየዘርፉ የተነሡትን ሀሳቦች ምላሽ በመሥጠትና በማጠናከር በቀጣይ የእቅድ አካል ተደርገው እንደሚወሰዱና የቀጣይ በጀት አመት የኮሌጁን የትኩረት አቅጠጣጫን በማስቀመጥ ግምገማዊ የእቅድ ፈፃፀም ሪፖርቱ ተጠናቋል።
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሐምሌ 11/2017ዓ.ም