ኮሌጁ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን በጄኔራል ካውንስሉ ገመገመ።
ሰኔ 25 ፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በጀተ ዓመት ባቀደው እቅድ መሠረት በማድረግ የተሰሩ ተግባራትን አፈፃፀማቸውን ለመገምገምና የቀጣይ ጊዜ አቅጣጫ ለመሥጠት በሚያስችል አግባብ የተለዩ ዲፓርትመንቶች አስተባባሪዎችና ዳይሪክተሮች የዘርፍ የእቅድ አፈፃፀማቸውን ካቀረቡ ቡኋላ የኮሌጁ የበጀት አመቱ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል።
በቀረቡ ሪፖርቶችም ሊካተቱ የሚገቡ ነጥቦችና መሥተካከልና መልሰው ሊታዩ የሚገቡ ነጥቦችን በጄኔረል ካውንስል አባላቱ ተነስቷል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ኮር አመራሮች የተነሱ ነጥቦች ላይ ምላሽ በመሥጠትና በሪፖርቱ ባልተካተቱ ነጥቦችና ቀጣይ መሥተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በመሥጠት ግምገማዊው ስልጠና ተጠናቋል።